መዝሙር (አድኚኝ እናቴ) March 24, 2019
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/
የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሃል እንድትሆኚን ኃይል
ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቊልና
ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና /፪/
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/
ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለሁ
ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛሽ ሆኛለሁ
ስቅበዘበዝ አይቶ ተስፋ የሰጠኝ
እግዚአብሔር ይመስገን ከአንቺ ያስጠጋኝ
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/
በሥጋ ደክሜ በነፍሴ እንዳልጠፋ
እማጸንሻለሁ ድንግል የእኔ ተስፋ
የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ
መልካም ሥራን መሥራት እኔ አስተምሪኝ /፪/
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/
አንቺ የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው
ከመካከል ገብተሽ ሙይ የጎደለውን
ሠርጉ ተደግሷል ጎብኝልን ጓዳውን /፪/
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/