መዝሙር (ጌታ ሆይ ውለታህ) April 7, 2019
ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል
ስለ ኃጢአቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል
ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል
ስለ ኃጢአቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል
ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ /፪/
ትንሹም ትልቁም /፫/ መድረሻውን ሲያጣ
ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ /፪/
ነፋሳት ሲላኩ /3/ መዓትን ለማዝነብ
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ /፪/
የት ይሆን መድረሻው /፫/ የት ይሆን መንገዱ
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ /፪/
የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሃል እንድትሆኚን ኃይል
ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቊልና
ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና /፪/
እንደ በደሌማ ከሆነ ቅጣቴ
አያልቅም ተነግሮ ብዙ ነው ጥፋቴ
እንጃልኝ ፈራሁኝ አዬ ሰውነቴ(፪)
እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ
ኀዘኔ ጭንቀቴ በጣም በዛብኝ
ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺው አማልጂኝ
ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጅሽ
እናቱ ነሽና እርሱ አያሳፍርሽ
እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ