የልደት ማታ መዝሙር (ትምክሕተ ዘመድነ) January 6, 2018

ትምክሕተ ዘመድነ /፪/ ማርያም እምነ
ማርያም ትምክሕተ ዘመድነ

የድኅነታችን ዓርማ የነፃነታችን
የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን
አንቺን ለእኛ ዘርን ባያስቀር
እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
ሁላችን በጠፋን ነበር

አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ
የጌዴዎንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ
የእኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ
የዋኅ ርግብ ከአበው ሥር የተገኘሽ
ዕፀ ሳቤቅ የሕይወት ሐረግ ነሽ

አዝ
አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይህችን ዓለም ሲቃኝ
ንጽሕት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንቺን ቢያገኝ
ትኅትናሽን ሕይወትሽንም ወዶ
ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ
አከበረሽ በፍጹም ተዋሕዶትምክሕተ ዘመድነ

አዝ
የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም
ከኃጢአት ከመርገም የዳነብሽ ዓለም
አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን
በሲኦል ውስጥ ተግዘን የኖርን
ድንግል በአንቺ ነፃነት አገኘን
አዝ