መዝሙር (አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ) February 11, 2018

አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ (፪)
በበደሌ ብዛት /፪/ አይተህ አትጣለኝ

ሳስበው በደሌ ብዙ ነው /፪/
ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ/፪/

አዝ..

እርቃኔን ቀረሁኝ ተገፈፈ ልብሴ
መድረሻው ጠፋብኝ ተጨነቀች ነፍሴ
የብርሃን ጸዳሌ ከዓይኔ ተገፈፈ
ከፊትህ ለመቆም ጉልበቴ ታጠፈ

አዝ

አልቻልኩም ደግፈኝ እንድቆም /፪/
ለገነት የበቃህ ያን ቀማኛ ሽፍታ
እኔንም ደግፈኝ አውጣኝ ከዛን ለታ

አዝ

ሳስበው በደሌ ብዙ ነው(፪)
በጨለማ ነፍሴን በላት ውድማ /፪/
ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ (፪)