መዝሙር (በእፀ መስቀል) March 25, 2018
በእፀ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ (፪)
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ
መስቀል አሲዘው ኪሪያላይሶ ወደ ጎልጎታ ኪሪያላይሶ
ሲገርፉህ ሲያዳፉህ ኪሪያላይሶ ስትንገላታ ኪሪያላይሶ
በእፀ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ (፪)
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ
ያንን አቀበት ኪሪያላይሶ ያንን ዳገት ኪሪያላይሶ
ጀርባህ ተገርፎ ኪሪያላይሶ ስትቃትት ኪሪያላይሶ
በእፀ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ (፪)
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ
አንተን እያዩ ኪሪያላይሶ ሴቶች ሲያለቅሱ ኪሪያላይሶ
እናቶች ቀርበው ኪሪያላይሶ ላብክን ዳበሱ ኪሪያላይሶ
በእፀ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ (፪)
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ
መስቀል አስይዘው ኪሪያላይሶ እንዲያ ሲያዳፉህ ኪሪያላይሶ
የቀሬናው ሰው ኪሪያላይሶ ስምኦን አገዘህ ኪሪያላይሶ