መዝሙር ( ባለውለታዬ) April 22, 2018
ባለውለታዬ (፪)
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አደርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘኝ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ (፪)
ባለውለታዬ (፪)
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘኝ ጌታዬ
መዓረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ (፪)
ባለውለታዬ (፪)
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ
ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ
በሠላም ሂድ ብሎ ምሮኛል ንጉሱ (፪)
ባለውለታዬ (፪)
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ
የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሰራልኝ ሥራ በእድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ (፪)
ባለውለታዬ (፪)
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ