መዝሙር (አዳምን ለማዳን) October 21, 2018
ሰአሊ ለነ ማርያም
አዳምን ለማዳን ሰው የሆነው ወዶ
ስደትን ጀመረ በፍቅር ተዋርዶ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ብርድ በጸናበት በክረምት ወራት
ልጅሽን ታቅፈሽ ተነሳሽ ስደት
ሰአሊ ለነ ማርያም
የሄሮድስ ጭፍሮች ከሐገር ሲያሳድዱሽ
ልጅሽን ታቅፈሽ እንባሽን አፈሰስሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ለምኝልን ማርያም ከአንድዬ ከልጅሽ ከመድኃኔ ዓለም
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ለእግዚአብሔር ፍጹም
ሰአሊ ለነ ማርያም
ሰሎሜና ዮሴፍን ዘመድ ኣግኝተሽ
ልጅሽን ታቅፈሽ ስደትን ጀመርሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ፍጡራን በሙሉ ከቤታቸው ሆነው
አንቺ መሰደድሽ ኧረ ለምንድን ነው
ሰአሊ ለነ ማርያም
ከረሃብ ጋር ጸሐይ አንዴት አረገሽ
ሀዘንሽን ልካፈል ስለሆንኩ ልጅሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
አንድ ፍሬ ሕጻን ትንሽ ብላቴና
እንዴት አቋረጥሽው በረሃውን ሲና
ሰአሊ ለነ ማርያም
ምን አለች ኮቲባ ያልታደለች ፍጡር
ጌታዋን ታቅፈሽ ስትዞሪ መንደር
ሰአሊ ለነ ማርያም
አንቺን የመሰለች አንዲህ መቸገሩ
ብሆትኚ ነው ክፉ ያዞረሽ ባገሩ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ብላ ተናገረች ምስጢሩ ሳይገባት
ውሃን ለመዘከር ልቧ ጨክኖባት
ሰአሊ ለነ ማርያም
ክፉም አልመለስሽ እንባሽን አፈሰስሽ
ለውሻ እራርተሽ ውሃን የተዘከርሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ድንገት ወንበዴዎች ደርሰው ሲይዙሽ
ከሰሎሜ ወስደሽ ልጅሽን ታቀፍሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
የሌሊት ቁርና የቀን ሀሩርን
የተቀበልኩብህ ላላድን ነውን
ሰአሊ ለነ ማርያም
እያልሽ አለቀስሽ ምርር ብለሽ
ፊቱ ላይ ወረደ የሐዘን እንባሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ልጄን ሲገድሉብኝ ከማይ በህይወቴ
እኔን ያስቀድመኝ ይቅረብልኝ ሞቴ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ያበሰረኝ መልአክ ትወልጂያለሽ ያለኝ
ዛሬ በስደቴ ይምጣና ያጽጽናናኝ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ብለሽ ማልቀስሽን ባስታወስኩኝ ጊዜ
ልቤ ይቃጠላል በሀዘን በትካዜ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ከዘመድ መለየት ከሀገር መውጣት
እንዴት ያሳዝናል የድንግል ስደት
ሰአሊ ለነ ማርያም
እንባሽ የወረደው አንደ ሐምሌ ደመና
ሐዘንሽ ልዩ ነው የእስራኤል መና
ሰአሊ ለነ ማርያም
ጥቂት እፎይ ያልሽው ያኔ በስደትሽ
ኢትዮጵያ ስትደርሺ ነበር የተጽናናሽ
ሰአሊ ለነ ማርያም
እንግዲህ አሳስቢ ድንግል ስደትሽን
የደረሰብሽን ረሃብ ጥምሽን
ሰአሊ ለነ ማርያም
ስደትሽን ላስብ ስደተኛ ነኝ
የሰማዩ ቤቴ የሚናፍቀኝ
ሰአሊ ለነ ማርያም
ነይ ነይ ነይ በረድኤት
በአማላጅነትሽ ይሰጠን ምህረት
ሰአሊ ለነ ማርያም
በይ በእናትነትሽ አመሌን ቻይው
ትኅትና እንደሆን ከተፈጥሮሽ ነው