መዝሙር (ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ) October 28, 2018


 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ

መኃ ፯ ፧ ፩
ኢሳይያስ ተንብዮልሽ
ፈጣን ደመና ያለሽ
ጌታን በጀርባሽ አዝለሽ
በግብፅ በረሃ የዞርሽ
የበረሃው ሙቀት ንዳድ
የሌሊቱ ግርማ ከባድ
በአራዊቱ ድምፅ ሁካታ
ልብሽ በጭንቅ ሲንገላታ

 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ

ስለልጅሽ ተርበሻል
ጥማትንም ተጠምተሻል
ድካም መንገድ እንግልቱ
እንዴት ቻልሽው አዛኝቱ
የልጅሽን ነፍስ የሻቱ
ጠላቶቹ ስለሞቱ
መሰደዱ ይበቃሻል
ቅድስት ሃገር ይሻልሻል

 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ

በኢትዮጵያም እለፊ
ደበረ ቁስቋም ላይ እረፊ
ለዘላለም ከብረሽ
በአርያም ንገሽ
 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ

የበደሌ ሸክም በዝምቶ
ብሰደድም ፅድቄ ጠፍቶ
በይ መልሽኝ ከደጃፍሽ
በክንዶችሽ እቅፍ አርገሽ
በአለም ስጓዝ አንቺን ትቼ
ከእኔ እርቆ ፍቅር ጣዕምሽ
በበደሌ በኃጥያቴ ዛሬም እንኳን ብሸሽ
ተመለስ(ሽ) በይኝ እመቤቴ በእናትነተሽ

 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ

ለአዳም ተስፋው መድኃኒቱ
ድንግል ማርያም አዛኝቱ
በሃዘንሽ በስደትሽ
ታጥቦ ይጥራ እድፌ በእባሽ
በቃ ዛሬስ ተሸነግኩኝ
እናቴ ሆይ በይ መልሽኝ
ፍቅርሽ ጣዕምሽ ታትሞብኝ
ዛሬ ድኅነት በአንቺ እንዳገኝ

 ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ
 ተመለሺ ሱላማጢስ እመቤቴ ተመለሺ
 የአባትሽን ቤት አትርሺ