Info from Seattle King County ኮሮናቫይረስ መረጃ ከሲያትል ኪንግ ካውንቲ


ኖቬል ኮሮናቫይረስ (COVID-19) ምንድን ነው?
ኖቬል ኮሮናቫይረስ (COVID-19) ከሰው ወደ ሰው የሚጋባ አዲስ ቫይረስ ነው። ባሁኑ ጊዜ በዩናትድ ስቴትስ እና ብዙ አገሮች ላይ ይገኛል። አብዛኛው የኮሮናቫይረስ ህመም ቀለል ያለ ትኩሳትና ሳል አለው። አብዛኛው የኮሮና ቫይረስ ህመምተኞች የሆስፒታል እንክብካቤ አያስፈልጋቸውም። የህክምና ባለሙያዎች በጣም ትኩረት አድርገውበታል ምክንያቱም ይህ አዲስ ቫይረስ ጥቂት ሰዎችን ከባድ ህመምንና የሳንባ ምችን ለአንዳንድ ሰዎች ያስከትላል፤ በተለይ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑና በሌላ ህመም የተጠቁ፣ በሽታ የመከላከል ስርዓት ደካማ የሆኑትንና እርጉዞችን ያጠቃል።

የ(COVID-19) ምልክቶች ምንድን ናቸው?
COVID-19 የተገኘባቸዉ ልጆች እና አዋቂዎች ለቫይረሱ ከተጋለጡ በጥቂቱ 2 ቀናት ዉስጥ እስካ 14 ቀናት ምልክቶች እንደምታይባቸዉ ተዘግቧል፡
* ትኩሳት
* ደረቅ ሳል
* የትንፋሽ እጥረት
በCOVID-19 የተያዙ ህፃናት አብዛኛውን ጊዜ ቀለል ያለ ምልክቶች እንደ ብርድ፣ ንፍጥ ወይንም የጉሮሮ ህመም አላቸው። አንዳንድ ልጆች በተለያየ ህመም ምክንያት እንደ ቀደም ያለ የጤና ዕክል ና ልዩ የጤና እንክብካቤ የምያስፈልጋቸዉ ከፍተኛ አደጋ ላይ ይሁኑ አይሁኑ አናቅም።

COVID-19 እንዴት ይሰራጫል?
የጤና ባለሙያዎች ይህ ቫይረስ እንዴት እንደሚሰራጭ እያጠኑ ናቸው። ለጊዜው ባለሙያዎች ቫይረሱ የታመሙ ሰዎች በሚስሉበት ጊዜ ሲያስነጥሱ ወይም ሲያወሩ ከትንፋሻቸው ጋር በሚወጣ ምራቅእንደምሰራጭ ያስባሉ።ቫይረሱ በቅርበት ባሉ ሰዎች አፍና አፍንጫ ላይ ልያርፍ ይችላል ወይንም ተቀራርበዉ ባሉ ሰዎች (በ6 ጫማ ርቀት ዉስጥ) ሰንባዎች ልተነፈስ ይችላል። ቫይረሱ ሊሰራጭ በተጨማሪ የሚችለው አንድ ሰው ኖቬል ኮሮናቫይረስ ያለበትን እቃ በእጁ በመንካት በዛው እጅ አይኖችን፣ አፍንና አፍንጫችንን ሲነካ ነው። ሰዎች ምልክቶችን ሲያሳዩ አስተላላፊ ልሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል።

ማነው በCOVID-19 ለከባድ ህመም ተጋላጭ የሆነዉ?
ለጊዜው ልጆች በዚህ ቫይረስ ለምደርስ ከባድ ህመም በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑ ቡድኖች ዉስጥ አይደሉም። አንዳንድ ልጆች በሌላ ህመም የተጎዱና በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆነ በጣም የመጎዳት እድላቸው በከፍተኛ ደረጃ ያሉ ዉስጥ ይመደባሉ።በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ላይ የተጋለጡ ናቸው የሚባሉት እድሜያቸው ከ60 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች፣ ቀደም ያለ የጤና ዕክል ያለባቸዉ ወይንም የህመም መከላከል አቅማቸዉ የደከመ እና ነፍሰ ጡሮች ናቸው::

Sources:
1. COVID-19 የህዝብ ጤና ምክረ ሀሳቦች
2. ስለ COVID 19 ለቤተሰቦች