በMinnesota’s Resettlement Network ሥር የተለያዩ ግልጋሎቶችን ለማግኘት

በMinnesota’s Resettlement Network ሥር የተለያዩ ግልጋሎቶችን የሚሰጡ ድርጅቶች ስላሉ የunemployement application, ለምግብ እና ገንዘብ እርዳታ፣ ሥራ ለማፈላለግ፣ የዜግነት ማመልከቻ ለመሙላት እና የርቀት ትምህርት ዙሪያ እርዳታ ለማግኘት እና ለመሳሰሉት በሚከተሉት ቁጥሮች በመደወል እርዳታ ይጠይቁ፦

በሜኔሶታ ሃገረ ገዢ የተላለፈውን ትእዛዝ Gov. Walz's Order May 13

ከሜይ 18 2020 ወይም ከግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ
በሜኔሶታ ሃገረ ገዢ የተላለፈውን ትእዛዝ እንዲያከብሩ እያሳሰብን ከዚህ በታች ያሉትን ማስታወሻዎች ይመልከቱ፣
** የችርቻሮ መደብሮች ፣ የገበያ አዳራሾች እና ሌሎች ዋና የአካባቢ ንግድ ሥራዎች የደህንነት ዕቅድ ካላቸውና እና ከ 50 በመቶ በማይበልጥ ይዘት ብቻ የሚሠሩ ከሆነ እንደገና ሊከፍቱ ይችላሉ።
** ምግብ ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ ሳሎን እና ስፖርት ቤቶች እንደተዘጉ ይቆያሉ።
** ሚነሶታዎች 10 እና ከዛ በታች እስከሆኑ ድረስ ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰብ ጋር መሰባሰብ ይችላሉ።
** ማህበራዊ ፣ ሲቪክ/የከተማ እና ሕዝብ አስተዳደር ፣ ማህበረሰብ፣ በእምነት ላይ የተመሠረተ፣ መዝናኛ፣ ወይም ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ከ 10 በላይ ለሆኑ ሰዎች የተከለከሉ ናቸው።
** እነዚህን ጤናማ ልምዶች መከተልዎን ይቀጥሉ፣
• እጅዎን ቶሎ ቶሎ/ብዙ ጊዜ ይታጠቡ
• የበሽታው ሕመም ስሜቶች ከተሰማዎት ይመርመሩ
• ማህበራዊ ርቀት ይጠብቁ
• ጭምብል ያድርጉ
• ሲቻል ቤት ይቆዩ

ሙሉ ትእዛዙን ለማየት ይህንን ይጫኑ (Click here for order)

Faith Community Health Program of the Holy Trinity EOTC, Minneapolis MN
የምእመናን ጤና አገልግሎት ክፍል health@minnesotaselassie.