መዝሙር (ደስ ይበለን) February 11, 2024 (First Mezmur)

ደስ ይበለን
==============
 ደስ ይበለን/2/
 አምላክ አለ መሐላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ስምህ

ምሕረቱን አይተናልና
አድርሶናል አምላክ በጤና
ይችን ዕድሜ የጨመረልን
ለንስኃ ጊዜ የሰጠን

 ደስ ይበለን/2/
 አምላክ አለ መሐላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ስምህ

ኃጢአትህን ይታገስሃል
በቸርነት አምላክ ያይሃል
ደስታ ነው በሰማያት
በአንድ ኃጥእ የፅድቅ ሕይወት

 ደስ ይበለን/2/
 አምላክ አለ መሐላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ስምህ

እልል በሉ የጎበኛችሁ
በምሕረት ዓይኑ ያያችሁ
በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ
አመስግኑ ዝምም አትበሉ

 ደስ ይበለን/2/
 አምላክ አለ መሐላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ስምህ

ድንግል ማርያም ትፀልያለች
ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች
በድንግል ክብር እንኖራለን
በጽኑ ፍቅር አንድ እንዲያደርገን

 ደስ ይበለን/2/
 አምላክ አለ መሐላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ስምህ

መዝሙር (ስምህ በሁሉ ተመሰገነ) February 4, 2024 (First Mezmur)

ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
==============
 ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
 ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
 አንተን ማወደስ ያስደስተናል
 ስምህን ማክበር ክብራችን ሆኖአል /2/

አምላክ ተመስገን በሰማያት
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት
ከህፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ
አንተን ማመስገን ይሁን የኛ ዕጣ /2/