መዝሙር (ምን ሰማህ ዮሐንስ) February 7, 2021 (Second Mezmur)

 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅጸን ሳለህ /፪/
 ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /፪/
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /፪/
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/፪/

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /፪/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /፪/

መዝሙር (ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል) February 14, 2021 (First Mezmur)

ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል
ይእቲኬ ቤተ ምስአል ዘአስተአጸቡ ታቀልል
ለኩሉ ፍጥረት ትተነብል በአክናፈ መላእክት ትትኬለል
ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፌል

ማርያም ድንግል መመኪያቸው የደናግል
እርሷም እኮ የምልጃ ቤት ናት የሚያስጨንቀውን የምታቀልል
ለፍጥረት ሁሉ ትማልዳለች በመላእክት ክንፎችም ትጋረዳለች
እርሷ ትበልጣለች ከኪሩቤል ደግሞም ትልቃለች ከሱራፌል

መዝሙር (ክነፈ ርግብ) February 7, 2021 (First Mezmur)

ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ ሐመልማለ ወርቅ /፪/
አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ አማን በአማን/፫/ ኢየኃልቅ ኪዳንኪ ወላዲተ አምላክ/፪/

እንደ ርግብ ክንፍ በብርም እንደ ተሰራች ጎኖችሽም የወርቅ ሐመልማል/፪/
አንቺ ምስራቅ ነሽ ልጅሽም የጽድቅ ፀሐይ ነው እውነት በእውነት/፫/ አያልቅም ቃል ኪዳንሽ የአምላክ እናት/፪/

መዝሙር (ሰአሉ ለነ) January 31, 2021 (Second Mezmur)

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን

አንተ የመረጥከውን ማን ይከሳል
ያጸደቅከውን ማን ይወቅሳል
ለሚገባው ክብርን መስጠት
ታዟልና በመጻሕፍት
ያከበርካቸው ባሪያዎችህን
እናከብራለን ቅዱሳንህን