መዝሙር (አብሰራ ገብርኤል ለማርያም) December 31, 2023 (Second Mezmur)

አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
==============
 አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
 ወይቤላ /፪/ ትወልዲ ወልደ


ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ
መንጦላእት ደመና ሰወራ
ንፅህት በድንግልና
አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔሀ

መዝሙር (ጻወዳጄ ሆይ) December 31, 2023 (First Mezmur)

ወዳጄ ሆይ
==============
 ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ
 የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ
 የተዘጋች መቅደስ ንጽሕት አዳራሽ

ሕዝቅኤል ያየሽ የምስራቋ በር
ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር
የልዑል ማደሪያ አማናዊት መቅደስ
ስለ ንጽሕናሽ ምስጋናን እናድርስ

መዝሙር (ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ) December 23, 2023 (Second Mezmur)

ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
==============
 ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
 በአካለ ስጋ ዕና በአካለ ነብስ
 በአካለ ነብስ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

የእግዚአብሔር አይኖቹ ጻድቃንን ከማየት
ጆሮቹም አይርቁም እነሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደረጋለች
በምልጃቸው እንመን አናመታ በአንዳች

መዝሙር (ሥላሴ ትትረመም) December 23, 2023 (First Mezmur)

ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
==============
  ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር /2/
ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ
ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ
ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ
ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ

  ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር /2/
ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል
በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል
ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል
ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል

  ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር /2/
በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል
በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል
ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት
በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት
አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት

  ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር /2/
በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ
ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ/2/

  ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር /2/
ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር
የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር
ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ
መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ

  ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር /2/