መዝሙር (ንጹም ጾመ) March 10, 2024 (First Mezmur)
ንጹም ጾመ
==============
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ/፪/
ወንትፋቀር/፬/ ንትፋቀር በበይናቲነ /፪/
ንጹም ጾመ
==============
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ/፪/
ወንትፋቀር/፬/ ንትፋቀር በበይናቲነ /፪/
ሰማይ ተከፈተ
==============
ሰማይ ተከፈተ ደስ ይበለን
ማሕሌት ተሰማ ደስ ይበለን
ዛሬ ተከበናል ደስ ይበለን
በመለኮት ግርማ ደስ ይበለን/2/
አምላካችን አንጻን እንጸልያለን
በእግዚያብሔር ቅዱሳን በግርማ ተከበን/2/
✟ሰላም ለኪ✟
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ
ማርያም እምነ ናስተበቍአኪ
እምአርዌ ነአዊ ተማኅፀነ ብኪ
በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ
ማኅበረነ ዮም (፫)ድንግል ባርኪ
✟አንደበቴም ያዉጣ✟
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከሃጢአት ፈላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በሀይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከኛጋ
አንደበቴም ያዉጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ ባይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሀይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
አስፈሪዉ ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ለጣኦት እንድንሰግድ ነገስታት ቢያዉጁም
ሁሉም ቢተወኚም ቢጠላኚም አለም
ፅናት ይሆነኛል ጌታ መድሀኒአለም
አንደበቴም ያዉጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ ባይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሀይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አብሬ
እርሱን ሳመሰግን ሚልኮን ብትስቅብኝ
ለጌታየ ክብር እዘምራለሁኝ
አንደበቴም ያዉጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ ባይኔ
በገባኦን ሰማይ ፀሀይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
ንፅሕተ ንፁሐን ከዊና
ከመ ታቦር ዘዶር ዘሲና
ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና ነበረት (2)
ሲሳያ ኅብስተ መና
ውስቴሃኒ ስቴ ጽሙና (2)