ቅዱስ ሰራባሞን የኒቅዩስ ሊቀ ጳጳስ - ሕይወቱና ተጋድሎው
- Details
- Created on Friday, 05 September 2014 02:33
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል ሓላፊ
ቤተ ክርስቲያን በዓላውያን ነገሥታት አሰቃቂ ስደት በደረሰባት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ምዕት ዓመታት ውስጥ ከተነሱት የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል አንዱ የሆነውና ለዛሬው የተጋድሎውን ዜና በአጭሩ የምንመለከተው ሰማዕት ቅዱስ ሰራባሞን ዘኒቅዩስ ነው። አባቱ አብርሃም ይባላል፤ አያቱ የቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ አጎት ሲሆን የተወለደው በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም ነው። ሲወለድ ወላጆቹ “ስምዖን” ብለው ስም አወጡለት፤ “ሰራባሞን” የጵጵስና...
ማቴዎስ ወንጌል
- Details
- Created on Wednesday, 03 September 2014 07:35
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም.
ምዕራፍ 7 ካለፈው የቀጠለ
ሠ. ሰፊ ደጅ የተባለች ባለጸጋን መጽውት ድኃን ጹም ማለት ነው፡፡
ሰፊ ደጅ የተባለች ፈቃደ ሥጋ ናት ወደ ሰፊው ደጅ የሚገቡ ብዙዎች ወደ ጠባቧ ደጅ የሚገቡ ደግሞ ጥቂቶች መሆናቸው ጌታን አያስቀናውም፡፡ ምክንያቱም ጥቂት ዕንቁ ያለው ደግሞ ብዙ ወርቅ ባለው፤ ጥቂት ወርቅ ያለው ብዙ ብር ባለው፤ ጥቂት ብር ያለው ብዙ ብረት ባለው፤ ጥቂት ብረት ያለው ብዙ ሸክላ ባለው አይቀናም፡፡...
ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን
- Details
- Created on Tuesday, 02 September 2014 07:13
- Written by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Sunday School Department Official Website
ከምንም የለንም ወደ ሚሊየን
የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዲስ ሕንጻ ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ አኖረ
-
የቤቶችና እና ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት ከመንግሥት ጋር በመሆን ሕንፃዎችን የማስመለስ ሥራ የሠሩትን አንጋፋ ሰዎች በዕለቱ ሸልሟል
በመምህር ይቅርባይ እንዳለ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ካሏት በርካታ ድርጅቶች መካከል ዋነኛውና አንጋፋዉ የልማት ድርጅት የቤቶች እና ሕንፃዎት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመነ ፕትርክና ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቷ የአዲስ አበባ ከተማን ያስዋቡና ለወደፊት የሀገራችን ዕድገት ምሳሌ በመሆ...
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ
- Details
- Created on Tuesday, 02 September 2014 07:11
- Written by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Sunday School Department Official Website
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጄኔብ ተካሄደ
የኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት በስሙ የመሠረታት ቤተክርስቲያን ናት ከተቋቋመችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ውስብስብ ችግር ቢያጋጥማትም ተግባሯ ሳይገታ ዓላማዋም ሳይዛነፍ ከዚህ ደረጃ ላይ ደርሳለች ወልድ ዋሕድ የሚለውን ቃል መሠረት አድርጋ አንድ እግዚአብሔር በሦስት ስም በሦስት ግብር በሦስት አካል አንድ አምላክ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከበረ ብላ ታስተምራለች፡፡ ሆኖም በሃይማኖቷና በነጻነትዋ ጸንታ የምትኖር በመሆንዋ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ የለም፡...
ማኅበረ ቅዱሳን 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሔደ
- Details
- Created on Tuesday, 02 September 2014 05:21
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 27 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
የማኅበረ ቅዱሳን 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ነሐሴ 24 እና 25 ቀን 2006 ዓ.ም. በማኅበሩ ሕንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሀገር ውስጥና የውጭ ማእከላት፤ የወረዳ ማእከላትና ግንኙነት ጣቢያዎች፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ተወካዮች፤ የማኅበሩ ሥራ አመራርና ሥራ አሥፈፃሚ አባላት፤ የማኅበሩ ልዩ ልዩ ክፍል ተጠሪዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት አካሄደ፡፡...
ማቴዎስ ወንጌል
- Details
- Created on Thursday, 28 August 2014 01:13
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 22 ቀን 2006 ዓ.ም.
ምዕራፍ 7
በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ ሰባት ውስጥ የሰውን ነውር ከማጋነን ይልቅ የራስን ባሕርይ መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን በሰፊው እንማራለን፡፡ ዋና ዋና አሳቦቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡
-
ስለ ፍርድ
-
የተቀደሰውን ለውሾች መስጠት እንደማይገባ
-
ዕንቁን በእሪያዎች ፊት ማስቀመጥ እንደማይገባ
-
ስለ ልመና
-
ስለ ጠባቧ ደጅ እና ስለ ሰፊው ደጅ
-
ስለ ሐሰተኞች ነቢያት
-
በዐለት ላይ ስለተመሠረተውና በአሸዋ ላይ ስለተመሠረተው ቤት
...
በግሪክ አቴንስ ዐውደ ርእይ ተካሔደ
- Details
- Created on Monday, 25 August 2014 10:52
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 19 ቀን 2006 ዓ.ም.
አውሮፓ ማእከል
በግሪክ አቴንስ ምክሓ ደናግል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ትምህርት ቤት ከማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል ጋር በመተባበር ከነሐሴ 9 እስከ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ዐውደ ርእይ ተካሔደ፡፡...
የግእዝ ሥርዓተ ንባብ (pronounciation)
- Details
- Created on Monday, 25 August 2014 04:47
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 19 ቀን 2006 ዓ.ም.
በመ/ር ደሴ ቀለብ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ መምህር
የግእዝ ሥርዓተ ንባብ ስምንት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
-
ማንሳት 5. ማናበብ
-
መጣል 6. አለማናበብ
-
ማጥበቅ 7. መዋጥ
-
ማላላት 8. መቁጠር ናቸው፡፡
...
“አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ.131፥8/
- Details
- Created on Wednesday, 20 August 2014 01:16
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም.
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሐ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባህርይ ዘተነድቀ ፤ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒሠቀ፤እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ፡፡ ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቊ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል፡፡...
ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም
- Details
- Created on Wednesday, 20 August 2014 00:47
- Written by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Sunday School Department Official Website
ዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም
የዜና ቤተክርስቲያን ሐምሌና ነሐሴ 2006 ዓ.ም ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ...
ማኅበረ ቅዱሳን በጀርመን ዐውደ ርእይ አካሔደ።
- Details
- Created on Wednesday, 20 August 2014 00:17
- Written by ቀዳሚ ገጽ
ነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም.
በጀርመን ቀጠና ማእክል
በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ሐምሌ 26 እና 27 2006 ዓ.ም በጀርመን ካስል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ሁኔታ፣ የማኅበረ ቅዱሳንን ታሪክ፣ አገልግሎትና በየጊዜው ያጋጠሙትን ችግሮች እንዲሁም የቤተክርስቲያን አገልግሎት በአውሮፓ በተለይም በጀርመን ያለበትን ሁኔታ፣ የአመሠራረት ታሪከ እና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ዐውደ ርእይ ተካሔደ።...
በዓለ ደብረ ታቦር
- Details
- Created on Monday, 18 August 2014 18:00
- Written by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Sunday School Department Official Website
በዓለ ደብረ ታቦር
በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፤
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
-
‹‹ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረድአነ፤
-
ወየብቡ ለአምላከ ያዕቆብ፤
-
ንሥኡ መዝሙረ ወሀቡ ከበሮ፤
-
መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ፤
-
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሰርቅ፤
-
በእምርት ዕለት በዐልነ፤
-
እስመ ሥርዓቱ፤ ለእስራኤል ውእቱ››
በረዳታችን፣ በረድኤታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ፤ ዝማሬውን አንሡ፤ ከበሮውንም ስጡ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆው ጋር በመባቻ ቀን በከፍተ...
አድርሺኝ
- Details
- Created on Monday, 18 August 2014 03:00
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 12 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
በጎንደር ከተማ በፍልሰታ ለማርያም ጾም ወቅት በካህናቱ፤ በሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና በምእመናን አማካይነት በየዓመቱ የሚከናወን የተለመደ ሥርዓት አለ፡፡ ይህም ሥርዓት “አድርሺኝ” በመባል ይታወቃል፡፡ በጎንደር ከነገሡት ነገሥታት መካከል ከ1703-1708 ዓ.ም. ለአምስት አመታት በንግሥና የቆዩት ዐፄ ዮስጦስ የጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያንን በመትከል የሚታወቁ ሲሆን፤ አድርሽኝ የተሠኘውንም ሥርዓት በእርሳቸው እንደተጀመረ ይነገራል፡፡
ሕግና ሥርዓት - በሐበሻ አሜሪካ
- Details
- Created on Friday, 15 August 2014 09:11
- Written by ዳንኤል ክብረት
ክረምት
- Details
- Created on Wednesday, 13 August 2014 07:25
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዕጉለ ቋዓት፥ ደስያት
ይህ ወቅት ከነሐሴ 10 እስከ ነሐሴ 27 ቀን ድረስ ያሉት 17 ዕለታት የሚጠሩበት ነው፡፡ ፍጥረታትና በባሕር የተከበቡ ደሴቶች የሚታወሱበት ጊዜ ሲሆን ወቅቱም ዕጓለ ቋዓት ደስያት ዐይነ ኩሉ ይባላል፡፡ ዕጓለ ቋዓት የሚለው ቃል ቁራን ሲያመለክት፣ ቁራ ሲወለድ ያለ ፀጉር በሥጋው ብቻ ይወለዳል፡፡...
ፍልሰታና ሻደይ
- Details
- Created on Monday, 11 August 2014 07:30
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 5 ቀን 2006 ዓ.ም.
ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ በመላው ዓለም የክርስትና እምነት በሐዋርያቱ መሰበክ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሀገራችን የክርስትና እምነት ተሰብኳል፡፡ በተለይም በሀገራችን የሰሜኑ ክፍል ህዝበ ክርስቲያኑ ለረጅም ዘመናት ሥርዓተ አምልኮ ሲፈጽምባቸው እንደነበሩና አሁንም አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ በአካባቢው የሚገኙ በርካታ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናትና መንፈሳዊ ቁሶች ያስረዳሉ። እነዚህም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ መንፈሳዊ ቅርሶች ናቸው። ከማይዳሰሱ መንፈሳዊ ቅርሶች መካከል የተለያዩ መንፈሳዊ...
ደብረ ታቦርና ቡሄ
- Details
- Created on Monday, 11 August 2014 06:50
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
ነሐሴ 5 ቀን 2006 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።...
ልጆችም ወላጆችም የሚተባበሩበት የፍልሰታ ለማርያም መታሰቢያ ጾምና በዓል
- Details
- Created on Friday, 08 August 2014 12:57
- Written by Hara Tewahido
(አለቃ አያሌው ታምሩ)
- በኢትዮጵያ እመቤታችንን መውደድ በልማድ እንደ ተረት በማይታይ ዓይነት ኹኔታ ተስፋፍቶ የኖረ አይደለም፡፡ ወንድም ሴትም ቢኾኑ እንዳላቸው የእምነት መጠን በእመቤታችን ስም ጸሎት ጸልየው፣ ስእለት ተስለው፣ ምጽዋት አድርገው፣ ዝክርዋን ዘክረው፣ ስምዋን ጠርተው፣ በአማላጅነትዋ ተማፅነው ዐሳባቸው እየተፈጸመላቸው፣ የጎደለው እየሞላላቸው፣ የጠመመው እየተቃናላቸው፣ ድውያን ፈውስ በማግኘት፣ ሠራተኞች ለሥራቸው የተቃና መንገድ በማግኘት፣ መምህራን በሚያስተምሩበት፣ ቅዱሳን ገድላቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜና ምክንያት ኹሉ የእመቤታችንን ረድኤት እ ...
ፍልሰታ ለማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
- Details
- Created on Thursday, 07 August 2014 06:45
- Written by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Sunday School Department Official Website
"ፍልሰታ ለማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ"
በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA in Philo)
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ "ወአመ በፅሐ ዕድሜሁ እግዚአብሔር ፈነወ ወልዶ ወተወልደ እምብእሲት፡- ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ" /ገላ. 4፡4/ በማለት እንደገለጸልን ፍጠረኝ ሳይለው ከብዝሐ ፍቅሩ የተነሳ የፈጠረው የሰው ልጅ በፈጸመው ስሕተት ወይ በደል ተጸጽቶ፣ በዕንባና በለቅሶ ተሞልቶ፣ ማቅ ለብሶና አመድ ነስንሶ በንስሐ ሕይወት...